Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በብራስልስ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከተለያዩ የአውሮፓ ኅብረት ተቋማት ሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
 
ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባላት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ የሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ማሪያ አሬና፣ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ኡርማስ ፔት እና የአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል ጃቪየር ናርት ጋር መክረዋል።
 
በውይይታቸውም ዶክተረ ጌዲዮን በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰቱት ግጭቶች እና በሀገሪቱ ስላለው ወቅታዊ ሠላምና መረጋጋት እንዲሁም መንግስት ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተገናኘ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የወሰዳቸውን እርምጃዎች አስመልክቶ ለፓርላማ አባላቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
የፓርላማ አባላቱ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ወቅታዊ መረጃ መለዋወጥ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
 
በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ መካከል በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዲፈጠር በቅርበት ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸውም መግለጻቸው ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ዶክተር ጌዲዮን ከሣምንት በፊት ከካርሎስ ዞሪህኖ የአፍሪካ፣ የካሪቢያን እና የፓሲፊክ መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ ፓርላማ ምክር ቤት ሰብሳቢ ጋር መወያየታቸውም ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.