Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴን ግድብ በተባበረው አንድነታችን፣ ክንዳችን እና ሀብታችን ሰርተን የምንጨርሰው መሆናችን እናረጋግጣለን- የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የምክክር መድረክ

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የምክክር መድረክ የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ወቅታዊ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ኢፍትሃዊ የሆነ ውሳኔ ለመወሰንና ለማስወሰን እንዳንድ ሀገራት የተዛባ ውሳኔ እንዲሰጥ ጫና ለመፍጠር እየጣሩ ይገኛሉ ብሏል፡

በአንድ ወቅት ተመሳሳይ የተዛባ ውሳኔ በ League of Nations ሲተላለፍ የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት የሚከተለውን ብለው ነበር፡፡

‹‹ሀገሬ ኢትዮጵያ በአለም ሸንጎ ላይ ፍርድ ተነፍጓት ስታዝን የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ ለነፃነቷና ለመብቷ ከኮሎኒያልስት ጣሊያን ጋር በየጊዜው ስትዋጋ ያሸነፈችውም ብቻዋን ነው፡፡ የተጠቃችውም ብቻዋን ስለሆነ ሀገሬ መቼውንም በሚደርስባት አደጋ ከማንም እርዳታ አገኛለሁ ብላ አትጠብቅም፡፡››

ዛሬም ሆነ ነገ ነፃነቷን ለመጠበቅ ታሪኳን ለማስከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ አለባት፡፡

እሷ እራሷ ብቻ ናት! እንዳሉት ሁሉ አሁንም ያለን ትውልዶች የተዛባውን ሚዛን ማስተካከል ያለብን እኛው ነን እና የአድዋውን ድል በተባበረው በአያቶቻችን ክንድ እዳሸነፍነው ሁሉ የህዳሴውንም ግድብ በተባበረው አንድነታችን፣ ክንዳችን እና ሀብታችን ሰርተን የምንጨርሰው መሆናችን እያረጋገጥን አቋማችንን በጋራ ስንገልፅ መነሻ ያደረግነው

1. የግድቡ መገንባት በአገሪቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ላይ ልዩነት እንደሌለው፣

2. ኮሎኒያሊስቶች አፍረካን እና ሀብቷን ለመቀራመት አውጥተውት የነበረና አሁን የሚያፍሩበት የ1029 እና የ1929 ዓ/ም ኢትዮጵያ ባልተወከለችበት የሕግ ተገዥ የምትሆንበት ሕጋዊም ሆነ አመክኒያዊ ነገር የሌለ መሆኑን፣

3. የሀገራችን ምሁራን በሰሯቸው ጥናቶች ግድቡ የሚገነባው ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ ባልሆነ ቦታ ከመሆኑ በተጨማሪ ውኃው ግብፅ ወይም ሱዳን ላይ ቢከማች ኖሮ በትንነት የሚባክነውን ውኃ ስለሚያስቀር ተመራጭ የሚያደርገው መሆኑን ነው፡፡

ከዚህ በላይ በቀረበው መነሻነትም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ባለ ስድስት ነጠብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

1. የጀመርነው እውን ለማድረግ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደምናደርግ እናረጋግጣለን፡፡

2. የህዳሴው ግድብ የአንድነታችን ተምሣሌት በመሆኑ በዘር፣ በኃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይኖር የመንግስትን አቋም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደግፍ እንጠይቃለን፡፡

3. እኛ ጠግበን በብርሃን እየኖርን እናንተ በረሃብና በጨለማ ኑሮ ከሚል እና እራስ ወዳድ አስተሳሰብን በፅኑ እናወግዛለን፡፡

4. እኛ የኢትዮጵያ የመንግስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን የየድርሻቸውን እንዲወጡና ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንደያሳድሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ ህዳሴ ላይ ሰሞኑን የወሰደውን ኢ-ፍትሐዊ ውሣኔ እየተቃወምን የአፍሪካ ህብረት እንዲህ ዓይነት ጣልቃ ገብነትን እንዲቃወምና መርህን እና ሕግን መሠረት በማድረግ ከኢትዮጵያ ጐን እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡

6. የአሜሪካ መንግስት በታዛቢነት ገብቶ ሀብት እና የዲፕሎማሲያዊ ኃይሉን በመጠቀም ወደ አደራዳሪነት እራሱን ከማሸጋገር በላይ የወሣኝነት ሚና ያለው የሚመስል መግለጫ ማውጣቱን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የምክክር መድረክ ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.