Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር ከ250 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አማራ ክልል በተለይ ሐምሌ 6 በሚያካሂደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከል መርሐ ግብር ከ250 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል ማቀዱንም ገልጿል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው እና የፌዴራል ፣ የክልል እና የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት አራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በጎንደር ዛሬ ተጀምሯል።

በአማራ ክልል በተያዘው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአጠቃላይ ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኝ ለተከላ ማዘጋጀቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጿል።

ለዚህ ዓመት አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ173 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል።

በአጠቃላይ ለተከላ ከተዘጋጀው ችግኝ ውስጥ ከ13 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኝ አትክልትና ፍራፍሬ ነውም ተብሏል።

ከ7 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ የቡና፣ ከ5 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የቆላ ፍራፍሬ እና ከ535 ሺህ በላይ የደጋ ፍራፍሬ ችግኞች መዘጋጀታቸውም ነው የተመለከተው፡፡

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.