Fana: At a Speed of Life!

የህግ ታራሚዋን አስገድዶ የደፈረው ፖሊስ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህግ ታራሚዋን በመድፈር የተከሰሰው ፖሊስ በዘጠኝ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።

ፍድር ቤቱ ትናንት ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ላይ በዋለው ችሎት ተከሳሹ ፖሊስ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

ፖሊሱ በምርመራ ሰበብ የህግ ታራሚዋን መድፈሩ በምስክሮችና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ በዘጠኝ አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

በችሎቱ የተሰየሙት ዳኛ እንደገለጹት÷ ድርጊቱ የተፈፀመው በምእራብ ሀረርጌ ዞን ሸነን ኡጎ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ነው፡፡

በግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የግል ተበዳይ የሆነችው የህግ ታራሚ እመረምርሻለሁ በሚል ሰበብ ወደ አዳራሽ በመጥራት ከፍተኛ ድብደባ ካደረሰባት በኋላ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡

የግል ተበዳይ ወደ መሰላ ማረፊያ ቤት በተዘዋወረችበት ወቅት በሰጠችው ቃልም÷ ፖሊሱ ይህን ጉዳይ ለሰው ብትናገሪ ለኔ ከጥፍሬ በታች ነሽ በማለት ያስፈራራት መሆኑንና ከፍተኛ ጥቃት ያደረሰባት መሆኑን ተናግራለች፡፡

በሰዎች ምስክር ማስረጃና ከጭሮ አጠቃላይ ሆስፒታል በተገኘ መደፈሯን በሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ጥፋኛ ሆኖ በመገኘቱ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.