Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ቁ ዶንግዩ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷በምግብ ምርትና ምርታማነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና ዘላቂ ልማትን ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን አሁን ላይ በኢትዮጵያ መንግስት እየተሰሩ የሚገኙ የበጋ መስኖ ስንዴ፣ አረንጓዴ ዐሻራ፣ የኢንዱስትሪ ልማት እና ሌሎች ፕሮጄክቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
አምባሳደር ሬድዋን ፋኦ በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ በቀጣይም ድርጅቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ቁ ዶንግዩ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እያሳረፈች ያለውን ደማቅ የአረንጓዴ ዐሻራ ተነሳሽነት እና መንግስት በግብርና ስርዓት ለውጥ ለማምጣት እያደረጋቸው ያሉትን ጥረቶችን አበረታተዋል ፡፡
ሁለቱ ወገኖች ምርታማነትን ለማሳደግ፣ አረንጓዴ ከተሞችን በመገንባት እና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸውን በጣሊያን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.