Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሠራዊት ላይ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎች የሚናፈሱት አፍራሽ ተግባራት ተገቢነት የጎደላቸው ናቸው – ብርጋዲየር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ያለምንም ልዩነት በሚያገለግለው መከላከያ ሠራዊት ላይ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች የሚናፈሱት አፍራሽ ተግባራት ተገቢነት የጎደላቸው መሆናቸውን ብርጋዲየር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ ገለጹ፡፡

ሀገር ጠባቂውን መከላከያ ሠራዊት ከአሉባልተኞች በመታደግ እየተጠናከረ የሚሄድ ተቋም የማድረግ ኃላፊነት ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ይጠበቃል ሲሉ የገለጹት የቀድሞ ሠራዊት አባላት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ÷ የሀገሪቱ ወታደር በዘመናት መካከል የሀገሩን ዳርድንበር እና ክብር በመጠበቅ ረገድ እያደረገ ያለው ተጋድሎ ትልቅ ነውና ሁሉም ዜጋ ይህን ተቋም ለመገንባት መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል።

ሌላኛው ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ ሠራዊት አባል ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ÷ ኢትዮጵያዊያን በነፍሱ ተወራርዶ ለሚጠብቃቸው መከላከያ ሠራዊት አሥፈላጊውን ክብር ሊሠጡት ይገባል ብለዋል።

በአፈወርቅ ዓለሙ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.