Fana: At a Speed of Life!

ጥራት ያለው ግብዓት ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪው ለማቅረብ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መሥራት አለባቸው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥራት ያለው ግብዓት ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ለማቅረብ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

የይርጋለም ግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለፋብሪካ የሚሆነውን ጥሬ እቃ ለማግኘት እያጋጠመው ያለውን ችግር ለመፍታት ከሲዳማ ክልል መንግስት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መምህሩ ሞኬ በይርጋዓለም ግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በግብዓት እጥረትና ጥራት ጉድለት ምክንያት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል።

የሳንቫዶ ፋብሪካ የእቃ አቅርቦት አስተባባሪ አቶ ሚሊዮን ቴጋ በበኩላቸው ÷ከግብዓት አቅርቦት በተለይም ጥራት ያለውን የአቮካዶ ምርት ዘይት ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ግብዓት ለማግኘት ይቸገራሉ ምክንያቱ ደግሞ ሕገወጥ ደላሎችና በአርሶ አደሩ ዘንድ ያለው የተሳሳተ አመለካከት መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በሕገወጥ ደላሎች በፈተጠረ ችግር ምክንያት የግብዓት እጥረት እንዳይከሰትና ሕገወጥ ደላሎችን ለመከላከል እንደሚሠራ የተናገሩት የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበር የገበያ ትስስሩ ጤናማ እንዲሆን መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ወደ ሥራ ከገቡ ማለትም በዋይ ቢ ኤም እና በ ኤስ ኤ ኤን ቪ ኤ ዲ ኦ አቮካዶ ዘይት ፋብሪካዎች ብቻ አምስት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል።

በታመነ አረጋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.