Fana: At a Speed of Life!

500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን ኮርፖሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስምንተኛ ዙር 500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ዛሬ ጠዋት ጅቡቲ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡

በዘንድሮው የምርት ዘመን ከውጭ እየተጓጓዘ ከሚገኘው ዩሪያ ማዳበሪያ ውስጥ 1 ሚሊየን 105 ሺህ 244 ኩንታል በቅርቡ በሁለት ዙር ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

የዛሬውን ጨምሮ እስካሁን ከውጭ እየተጓጓዘ የሚገኘው ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ መጠን ወደ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ማደጉም ነው የተገለጸው።

ለዘንድሮ የሰብል ዘመን ‘ፈርቲግሎብ’ ከተባለ የውጭ ኩባንያ የተገዛው ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ መጠን 5 ሚሊየን 1 ሺህ 100 ኩንታል መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በምርት ዘመኑ ከውጭ ከገዛው 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከጥር እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ 11 ሚሊየን 771 ሺህ 376 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፥ እስካሁን 10 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ለአርሶ አደሩ እየቀረበ እንደሚገኝ መገለጹን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.