Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሰኔ 19፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች የሕዝብ ለሕዝብ የሰላም መድረክ በከሚሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ከሦስቱም ዞኖች የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የሰላም መድረኩ÷በሃይማኖት አባቶች ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ ከድጃ አሊ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ለዘመናት በአብሮነት የኖረውን የአጎራባች ዞኖች እና ወረዳዎች ማህበረሰብ እሴት አሁንም ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው÷ ለዚህ ደግሞ የሰላም መድረኩ ተሳታፊዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአሸባሪው ህወሓት የእኩይ ድርጊት ተባባሪ የሆነው ሸኔ በሕዝባችን ላይ ያደረሰው ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ አሸባሪዎችን በጋራ በመታገል ለጋራ ልማታችን አብረን መቆም አለብን ብለዋል፡፡

 

በእሸቱ ወልደሚካኤል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.