Fana: At a Speed of Life!

ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ኦይል ሊቢያ ማደያ ታሸገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን በወናጎ ከተማ ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ኦይል ሊቢያ ማደያ ማሸጉን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ምስጋና በራሶ÷ መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የነዳጅ አቅርቦት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ከወናጎ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት ከህዝቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ነዳጅ ለማጣራት በተደረገ ክትትል ቤንዚኑ የጥራት ጉድለት እንዳለበት ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል።

የወናጎ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ጎሎ በበኩላቸው÷ በከተማዋ እየተበራከተ የመጣውን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴና ከደረጃዎች በታች የሚመጡ ምርቶችን የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል ።

በዚህም መሠረት ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ በኦይል ሊቢያ ማደያ ላይ ጥልቅ ክትትል በማድረግ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን አመላክተዋል ።

ህገ-ወጥ ተግባራትንና መሰል ችግሮች ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ ከዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የክትትል ስራ አጠናክረው ተጠናክሮ ይቀጥላል መባሉን ከደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.