Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የአድዋ 00 ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ያጠናቀቀውን መደበኛ ስብሰባ ተከትሎ አባላቱ የአረንጓዴ አሻራ ካኖሩ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ያለውን የአድዋ 00 ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳትፎ አድርገዋል።

በመቀጠልም በግንባታ ላይ ያለውን የአድዋ 00 ፕሮጀክት ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጉብኝቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለ ፕሮጀክቱ ዓላማ፣ ይዘትና ፋይዳ እንዲሁም አሁን ስላለበት ደረጃ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሀገራዊ የሰላምና ደህንነት፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማሳለፍ ውይይቱን አጠናቋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.