Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ሸኔ ላይ ሰፊ ዘመቻና እርምጃ እየተወሰደ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ሸኔ ላይ ሰፊ ዘመቻ እና እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፥ የሽብር ቡድኑ ሽኔ እየተሸነፈ መሄዱን ተከትሎ የክልሉን ስፋትና የህዝብ አሰፋፈር በመጠቀም ችግሮች መፍጠሩን አብራርተዋል።

ሸኔ በተለይም የአማራ እና አሮሞ ብሄሮችን በማጋጨት፣ ፍርሃትን በማንገስ እና ነውጥ በማስነሳት ኢትዮጵያን ለማዳከም መስራቱን ተናግረዋል።

እነዚህ አካሄዶቹ መክሸፋቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

ሸኔን በመዋጋት የጸጥታ አካሉና የክልሉ ህዝብ እያደረጉት ላለው ትግል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የ2014 ዓ.ም የስራ ዘመን ስኬትና ተግዳሮቶችን በማንሳትም ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተስፋዬ ከበደ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.