Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ ባለ 5 ወለል ህንጻ የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጌጃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ባለ 5 ወለል ህንጻ የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀመሩ።

ከንቲባዋ ግንባታውን ባስጀመሩበት ወቅት፥ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍና ለነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እፎይታን ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

“ማድረግ የምንችለውን ነገር ሁላችን ስናደርግ ህዝባችን ተስፋው ይለመልማል፤ ጠንክሮም ይሰራል” ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ የአካባቢው ነዋሪ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ፤ እንኳን ልማት መጣልን የሚል ምላሽ ካየንባቸው አካባቢዎች አንዱ በመሆኑ÷ ሙሉ ለሙሉ ሞዴል አድርጎ ለመውጣት በምገባ ማእከል፣ የመኖሪያ ቤት፤ የመስሪያ ቦታ፤ የከተማ ግብርና አጠቃላይ ስራዎች ተሳልጦ እየሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ሌሎችም ባለሃብቶች የብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽንን ተሞክሮ በመውሰድ ለአካባቢያችሁ የምትችሉትን ታደርጉ ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ በዚህ ወቅት÷ ከተለመደው የግንባታ ሂደት ወጣ ያለ ዘመናዊና ያማረ ስራ እንሠራለን ብለዋል፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው÷ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ነድፈን እየሰራን ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች በልደታ ክፍለ ከተማ በ60 ቀናት የጓሮ አትክልት ልማት ስራዎች የደረሱ አትክልቶችን ለአካባቢው ማህበረሰብ የማእድ ማጋራት አከናውነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.