Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ ከመሰረት ልማት ግንባታ ባሻገር በእውቀት ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ ከመሰረት ልማት ግንባታ በተጨማሪ በእውቀት ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

ሁዋዌ ቴክኖሎጂ የ2022 የኢትዮጵያ አጋርነት ሰብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ÷ሁዋዌ  ከመሰረት ልማት ግንባታ ባሻገር የእውቀት ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው÷የእውቀት ሽግግሩም የአገር ውስጥ ተቋማት ዲጂታል የንግድ ስርዓቶችን እንዲረዱና የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲያሳኩ ያግዛል ብለዋል፡፡

የሁዋዌ ኢትዮጵያ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኮዊን ካኦ በበኩላቸው÷ ህዋዌ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ከ158 የአገር ውስጥ አጋሮች ጋር በመስራት ለ3ሺህ 700 ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

ሁዋዌ በኢትዮጵያ፣ ለኢትዮጵያ በሚል እየሰራ መሆኑን ያብራሩት ምክትል ስራ አስፈፃሚው÷ የስራ እድል ከተፈጠራላቸው ውስጥ 70 ከመቶዎቹ የአገር ውሳጥ ዜጎች ናቸው ብለዋል።

ሁዋዌ በኢትዮጵያ በ23 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የዲጂታል አካዳሚ ያለው ሲሆን÷ ተማሪዎች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ብቁ እውቀት እንዲጨብጡ እያስቻለ ነው ተብሏል።

ሁዋዌ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የምታስተናግደውን 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ለመደገፍ ቃል መግባቱንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.