Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የ900 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የአማራ ክልል ቅርንጫፍ በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ባለፉት 11 ወራት 900 ሚሊየን ብር የሚገመት ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።

ማህበሩ ካደረገው ድጋፍ ባሻገር 209 የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ማገናኘቱንም ነው የጠቆመው።

በክልሉ በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምግብ ነክ ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የሕክምና ድጋፎች ማድረጉንም አመላክቷል።

የቅርንጫፉ የኘሮግራም አስተባባሪ አቶ አለበል ቢያድግልኝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷ ጉዳት ለደረሰባቸውና ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰቦች ለሆኑ 30 ሺህ ያህል አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

የክልሉ ቀይ መስቀል ማኅበር ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ኮሚቴ ጋር በጥምረት ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ባለሙያዎች በሰብዓዊነት እና በዓለም አቀፍ ስምምነት ላይ ሥልጠና ሰጥቷል።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.