Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለረጅም ጊዜ ዕድሳታቸው ሲጓተት የነበሩ የቴአትር ቤቶችን ስራ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለረጅም ጊዜ ተጓቶ የነበረውና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙውን የአዲስ አበባ ሕጻናትና ወጣቶች ቴአትርና የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን ወቅታዊ የዕድሳት ሥራ ጥቅል አፈጻጸምን ጎብኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች ሁለቱም የቴአትር ቤቶች ፕሮጀክቶች ከትውልድ የስብዕና ግንባታ አስፈላጊነታቸው አኳያ በተያዘላቸው በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁና ተግዳሮቶችን ለመፍታት ብሎም ለታለመላቸው የትውልድ ግንባታ መዋል እስኪችሉ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።
የሕዝባችንን የለውጥ ፍላጎት በሁሉም ረገድ ዕውን ለማድረግ አንድን ፕሮጀክት ስንጀምር በቅንጅት እስከምናጠናቅቅበት ጊዜ ድረስ በባለቤትነት ስሜትና በኃላፊነት መሥራት ይኖርብናልም ነው ያሉት፡፡
 
ትውልድ አገሩን እንዲወድ አድርጎ አንጸ ለመገንባትም መሠል የጥበብ ተቋማት አስተዋጽኦቸው የጎላ እንደሆነ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በመላው አዲስ አበባ የጥበብ ስራዎችን በመደገፍ የሀገራችንን ቴአትርና ቱሪዝም ለመለወጥ እንዲቻል ከለውጡ ማግስት አንስቶ10 አንፊ ቴአትሮች የተገነቡ ሲሆን÷ጥሩቱ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.