Fana: At a Speed of Life!

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በ11ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በፖላንዷ ካቱቬሰ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 11ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው ዓለም አቀፍ ፎረሙ ከተሞችን ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር የተሻለ ህይወትን ለማስፈን በሚያስችሉ መንገዶች ላይ የሚመክር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ ከዓለም የተወጣጡ የአገራት መሪዎች ፣ የዘርፉ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ ሀላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎች በተገኙበት በከተሞች ልማት ነባራዊ ሁኔታና የነገ መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የልምድ ልውውጥ የሚደረግባቸው መድረኮችም ለአገራችን ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ እንደሆኑ እምነታቸው መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በ11ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.