Fana: At a Speed of Life!

በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞች የሚተከሉት በሴቶች ይሆናል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞች በሴቶች እንደሚተከል የብልፅግና ፖርቲ የሴቶች ሊግ አስታወቀ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ከነገ ጀምሮ አንደኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ ያካሂደል ።

ይህንንም ምክንያት በማድረግ የሊጉ አባላት ዛሬ በሀዋሳ በተለምዶ አሞራ ገደል በሚባል ቦታ ችግኝ ተክለዋል።

የፓርቲው የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ ሴቶች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ እያሳረፉ ነው ብለዋል።

ባለፉት ሶስት አመታት 4 ቢሊየን ችግኞች በሴቶች ተተክለዋል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ በዘንድሮ አመት ብቻ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞችን በሴቶች ለመትክል እቅድ ይዘናል ብለዋል።

ሴቶች ከጓሯቸው ለምግብነት የሚያገለግሉ ችግኞችን እንዲተክሉ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ያነሱት ፕሬዚዳንቷ፥ ለዚህም ደግሞ የግንዛቤ ስራ በየአካባቢው እየተከናወነ ቆይቷልም ነው ያሉት ።

የብልፅግና ፖርቲ የፖሊቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ በበኩላቸው፥ “የተተከሉ ችግኞች ልንከባከብ እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚተጉ ክፉዎችን ደግሞ ልንነቅል ይግብል” ሲሉ ለሴቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ ማካሄዱ ለከተማዋና ለሲዳማ ህዝብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው በሴቶች ሊግ ለተደረገው የችግኝ ተከላ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.