Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው ፀሐፌ ተውኔትና ተዋናይ ሰለሞን አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ ሰለሞን አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በ “አብዬ ዘርጋው” የሬዲዮ ድራማ ይበልጥ የሚታወቀው ሰለሞን አለሙ÷ በአምስት ቋንቋዎች ከ500 በላይ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የመድረክ ቴአትሮችን እና መነባንቦችን ሰርቷል።
ለአብነትም፥ ከዳንኪራው ጀርባ፣ ፍራሽ ሜዳ፣ ገመዱ እና አዙሪትን የመሳሰሉ ተወዳጅ ስራዎች አበርክቷል።
በኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ በተለይ ከ1975 እስከ 1980 ገናና ስራዎችን ያበረከተበት ወርቃማ ዘመኑ ነበር።
ሰለሞን በቅርቡ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሌሊቱን ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.