Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ የግጭት መከላከልና ሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የግጭት መከላከልና ሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ የፌዴራል እና የክልል ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላትና አመራሮች፣ የሁሉም ክልልሎች ምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥና በተለይም በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን አስቀድሞ መከላከል ብሔራዊ የግጭት መከላከል አፈታት እና የሰላም ግንባታ ስትራቴጅ ሰነድ መዘጋጀቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡
ሰነዱን በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አማካኝነት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ በአሁኑ ወቅት አገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ምክንያቱም በአንዳንድ ክልሎችና አካባቢዎች ብሔርንና ማንነትን መሰረት ያደረገ ከሀብት ሽሚያ፣ ከመልካም አስተዳደር ጉድለት፣ ከተጎራባች መስተዳድሮች ወሰንና ማንነት እንዲሁም ከሌሎች ምክንያቶች ጋር በተያያዘ አለመግባባቶችና ግጭቶች እየተከሰቱ በመሆኑ ነው ብለዋል አፈ ጉባዔው፡፡
ለዚህ ችግር መፍትሔ የሚሆን የአስተዳደር ስርዓት መዘርጋት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላም ሰነዱን የማጽደቅ ሥራ እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.