በሲዳማ ክልል በዘንድሮው በጀት ዓመት የተሰሩ የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በዘንድሮው በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች የተሰሩ የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ይገኛሉ።
በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አስተዳደሮችና የከተማ አስተዳደሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!