Fana: At a Speed of Life!

የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ መወሰን የሚችሉ ጠንካራ ዜጎችን ለማፍራት የትምህርት ጥራት ስብራትን መጠገን ያስፈልጋል – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዕውቀት የበሰሉ፣ በሞራል የበለፀጉ፣ የሀገሪቷን የወደፊት ዕጣ መወሰን የሚችሉ ጠንካራ ዜጎችን ለማፍራት የትምህርት ጥራት ስብራትን መጠገን ያስፈልጋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ፡፡
ፕሮፌሰሩ ብርሃኑ ነጋ÷ በቀጣይ አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመፍታት መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በሀገሪቱ እየተስተዋለ ያለው የትምህርት ጥራት ስብራትና ውድቀት ለሀገር ውድቀት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው÷ ለዚህም ምክንያት ናቸው የተባሉ ጉዳዮችን የመለየት ሥራዎች እየተሠሩ ነው ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
በሀገሪቱ ሲተገበር የነበረው የትምህርት ሥርዓት የትምህርት ተቋማትን በማስፋፋት ላይ እንጂ ጠንካራ ዜጋን ማፍራት በሚችሉ ምሁራንና የትምህርት ግብአቶችን ማሟላት ላይ ያተኮረ አለመሆኑ ለትምህርት ጥራቱ ውድቀት ምክንያት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
በዕውቀት የበሰሉ፣ በሞራል የበለፀጉ ፣የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ መወሰን የሚችሉ ጠንካራ ዜጎችን ለማፍራት የትምህርት ጥራት ስብራትን መጠገን የሁሉም ኃላፊነት ስለመሆኑም ፕሮፌሰሩ አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ በበጀት አመዳደብ ላይ የሚታዩ ችግሮች፣ የመምህራን ጥቅማ ጥቅም በተገቢው አለመሟላት፣ ስርዓተ ትምህርቱ በሀገር በቀል ዕውቀቶች ያልተመሠረተ መሆኑ የሚሉትንና ሌሎችንም ለትምህርት ጥራት ችግር መነሻ ናቸው ያሏቸውንና በሚኒስቴሩ ሊፈቱ ይገባል ያሏውን ጉዳዮች አንስተዋል።
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራት ችግር ለመፍታት የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ተብራርተዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.