Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ለሶማሌ ክልል የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመከላከልና የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በተባበሩት መንግስት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የአደጋ ጊዜ ምላሽ አስተባባሪ ፒቴ ማንስፊልድ ከሚመራ ከፍተኛ የለጋሽ ድርጅቶች ልዑካን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በክልሉ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ተጽዕኖ ሁኔታ፣ በድርጅቱና በክልሉ መንግስት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።

በዚህም የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ÷ የክልሉ መንግሥት በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ በህብረተሰቡ ላይ በተለይም በህጻናትና ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ችግር እንዳያመጣ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግስት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት የአደጋ ጊዜ ምላሽ አስተባባሪ ፒቴ ማንስፊልድ በበኩላቸው÷ ድርጅታቸው ከመንግስት ጋር በመሆን ተማሪዎች በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይጠፉ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

እንዲሁም ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻልና የትምህርት ደረጃን ለማሳደግ እየተከናወነ ላሉ ሥራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገራቸውክ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.