Fana: At a Speed of Life!

በምክትል አፈ-ጉባዔ የተመራው ልዑክ በፓን-አፍሪካ ጉባዔ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ የተመራው ባለአምስት አባላት ልዑክ ፤ በፓን-አፍሪካ ፓርላማ ጉባዔ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ዛሬ በተጀመረው ጉባዔ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር አቶ ሙሣ ፋቂ ማሃማት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ አዳዲስ የአህጉራዊው ምክር ቤት አባላትም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

የፓን-አፍሪካ አመራሮች ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎች ምርጫ ለማካሄድ በሚቻልበት ሁኔታ ለጉባዔው ቀርቦ እንዲወሰን ክርክር እየተደረገ ይገኛል።

ምርጫው ለአምስቱም የአፍሪካ ቀጠናዎች ፍትሐዊ ውክልና እንዲኖር ያስችል ዘንድ ለአፍሪካ ሕብረት ፓርላማ የወቅቱ ኃላፊዎች ሃሳብና የምርጫ ማስፈጸሚያ አማራጭ መንገዶች ቀርበዋል።

ለስድስት ቀናት የሚቆየው የሕብረቱ ፓርላማ ጉባዔ፥ በተቀመጡት አቅጣጫዎች መሠረት በበርካታ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.