Fana: At a Speed of Life!

የካፋ ዞን በ58 ሚሊየን ብር ወጪ የገዛቸውን የእርሻ ትራክተሮች ለወረዳዎች አከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ ዞን አስተዳደር የዞኑን አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ 25 ትራክተሮችን ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አከፋፍሏል፡፡

የእርሻ የሜካናይዜሽን እርሻ ለማስፋፋት ያግዛሉ የተባሉት የእርሻ ትራክተሮቹ ከ58 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውና ወጪውም በዞኑ መንግስት በኩል እንደተሸፈነ ተገልጿል።

ትራክተሮቹም በዞኑ ለሚገኙ 12 ወረዳዎችና 5 ከተማ አስተዳደሮች ተበርክተዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፥ የእርሻ ትራክተሮች ከኋላ ቀር አስተራረስ ወደ ሜካናይዜሽን ለመሸጋገር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልፀዉ በቀጣይ ጊዜያትም መሰል ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በርክክብ ስነስርዓቱ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፥ ዞኑ ወደ ሜካናይዜሽ እየሄደ ያለበትን መንገድ አድንቀው ሌሎች ዞኖችም ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተከፋፈሉት ትራክተሮች በዞኑ በአመት ውስጥ ከ38 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ለማረስ እንደሚያስችሉ ተገልጿል።

በአብዱ ሙሃመድ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.