Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ለከተሞች ዘላቂ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል- ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ለከተሞች ዘላቂ ልማት ዕቅድ በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ፡፡

11ኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በፖላንዷ ካቱቬሰ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ሚኒስትሯ በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷የኢትዮጵያ መንግስት የከተሞች መስፋፋት ለኢኮኖሚ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ሙሉ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በሚያስችል መልኩ ከተሞችን ለመምራት የሚያስችሉ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንና ብሔራዊ የከተማ ልማት ፖሊሲም እየተከለሰ መሆኑን ተናገረዋል።

ዘላቂ የከተማ ልማት ለማህበራዊ ትስስር፣ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ ለሆነ የከተሞች ብልፅግና እና ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂ እና የማይበገር የከተማ ልማት ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ አዲሱን የከተማ አጀንዳ እውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃም የከተማ ልማት ኢንቨስትመንት ዕቅድ ከ ዩኤን ሃቢታት ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ መሆኑን ወይዘሮ ጫልቱ መጠቆማቸውን ከከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተሞች ለዜጎች የተሻሉ የመኖሪያ ሥፍራዎች ይሆኑ ዘንድ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረው፤ በእነዚህ የትብብር ዘርፎች እየተካሄዱ የሚገኙት ድጋፎችና ፕሮጀክቶችም የከተሞች አስተዳደሮችንና የከተሞችን መልካም አስተዳደር ተግባራትን ለማጠናከር እንዲሁም ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ለማስፈን አጋዥ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአጋር አካላት በቀጥታ በሚደረጉ የገንዘብ ድጋፎችም ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣ የከተማ ሴፍቲኔት እና ጠንካራ ከተሞችን ለመፍጠር በሚያስችሉ ተግባራት ላይ እየዋለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.