Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህሬን አቋርጦት የነበረውን በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህሬን አቋርጦት የነበረውን በረራ በዚህ ሣምንት መጨረሻ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት መሪ አምባሳደር አወል ወግሪስ በባህሬን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ወኪል አቶ ሰለሞን ዳዊትና ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሣምንት 3 ቀን ወደ ባህሬን የሚያደርገውን በረራ በዚህ ሣምንት መጨረሻ በፈረንጆቹ እንደሚጀምር ተገልጿል።
አየር መንገዱ በኮቪድ – 19 ምክንያት በረራውን አቁሞ የነበረ ሲሆን÷ በረራውን እንደገና መጀመሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ያጠናክል ተብሏል፡፡
በተለይም ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው ሲሄዱ ሲደርስባቸው የነበረውን እንግልት ያስቀራል ሲሉ አምባሳደር አወል ወግሪስ መናገራቸውን በባህሬን ከኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.