አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ተወያዩ።
ቋሚ ኮሚቴዎቹ በበጀት ዓመቱ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን አፈፃፀም ጎብኝተዋል፡፡
ኮሚቴዎቹ የልማት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም አስመልክተው ለርዕሰ መስተዳድሩ ገለፃ ማድረጋቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።