Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙ የሽብር ቡድኖች ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙ የሽብር ቡድኖች ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
መንግስት ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የህግ ማስከበር እርምጃ በመውሰደ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት መቻሉን ጠቅሰው፥ የህግ ማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
እርምጃ የተወሰደባቸው የሽብር ቡድኖች በየቦታው ችግር እየፈጠሩ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ሰሞኑን በወለጋ የተካሄደው ጭፍጨፋ አንዱ ማሳያ መሆኑንም አመላክተዋል።
ከዚህ ባለፈም በጋምቤላ ክልል የነበረውን የሽብር ቡድኑን ሴራን በማክሸፍ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሰላም መመለሱን አስታውቀዋል።
በኦሮሚያ፣ በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚወሰዱ የህግ ማስከበር ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑንም አስረድተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ከስር ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱ :-

 

https://www.youtube.com/watch?v=f4LUmGzpc4Y

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.