Fana: At a Speed of Life!

ለዓባይ ወንዝ አንዲት ጠብታ የማታበረክተው ግብፅ 100 በመቶ የወንዙን አጠቃቀም የመወሰን መብት ልትጠይቅ አትችልም -ቲቦር ናዥ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓባይ ወንዝ አንዲት ጠብታ የማታበረክተው ግብፅ 100 በመቶ የወንዙን አጠቃቀም የመወሰን መብት ልትጠይቅ አትችልም ሲሉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ገለጹ።

ቲቦር ናዥ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአባይ ግድብ ፍላጎት ላይ የሚደረጉ ድርደሮችን እና ውይይቶችን እንደሚከታተሉ ገልፀዋል፡፡

ነገር ግን መሰረታዊው እውነት ለዓባይ ወንዝ አንዲት ጠብታ የማታበረክተው ግብፅ 100 በመቶ የወንዙን አጠቃቀም ለመወሰን የመጠየቅ መብት እንደሌላት ነው።

ዲፕልማቱ አለም መለወጧን ግብፅ ማወቅ እንዳለባትም ነው ያስገነዘቡት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.