Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ውይይት ሳይዘገይ መተግበር ለመላው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን፣ እርቅ እና ብልጽግናን ያሳካል- የጀርመን መንግስት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ግጭት ለመቋጨት በኢትዮጵያ መንግስት እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እርምጃዎች ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ይወስዳሉ ሲል የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታ የሰላም ውይይት አስፈላጊ መሆኑን አንስቷል፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ለመቋጨት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እየተተገበሩ ያሉ አዳዲስ እርምጃዎች ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እንደሚወስዱም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

የሰላም ውይይት ሳይዘገይ መተግበሩም ለትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን፣ እርቅን እና ብልጽግናን እንደሚያሳክም አመላክቷል።

 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.