Fana: At a Speed of Life!

ለሶስት ወራት ሲካሄድ ለቆየው የፅዳት ንቅናቄ የከተማ አስተዳደሩ እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለሶስት ወራት ሲካሄድ ለቆየው የፅዳት ንቅናቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እውቅና ሰጥቷል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በዚህ ወቅት እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት የተደረገው የፅዳት ዘመቻ ከተማዋን ንጹህና ፅዱ ለማድረግ ለሚደረገው ጥረት ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

ንቅናቄው በየክፍለ ከተማው በብሎክና በትምህርት ተቋማት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን በዘመቻው ከተማዋን የማፅዳት ልምድን ማስፋት መቻሉን አቶ ጥራቱ አንስተዋል፡፡

ይህ የፅዳት ዘመቻ አሁን ያለንበት ወቅት ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ቦዮችን እና የወንዝ ዳርቻዎችን በማፅዳት በጎርፍ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.