Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ አርሶ አደሮች የ17 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ምርጥ ዘር አከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ አርሶ አደሮች 17 ሚሊየን ብር ግምት ያለው 3 ሺህ 416 ኩንታል ምርጥ ዘር አከፋፈለ።

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ለማ እንደገለጹት÷ ምርጥ ዘሩ በዘንድሮው የመኸር እና በልግ ወቅት ለተጎዱ የምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖችን ጨምሮ ለሐረሪ ክልል አርሶአደሮች ይዳረሳል፡፡

የዞኑ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ንጋቱ በበኩላቸው÷በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባጋጠመ የዝናብ እጥረት ምክንያት የበልግ ግብርና 90 በመቶ እንዲሁም በመኸር ግብርና 40 በመቶው ምርት ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ፅህፈት ቤቱ ከተለያዩ ለጋሽ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተከፋፈሉት 3 ሺህ 416 ኩንታል ምርጥ ዘርም÷ ስንዴ፣ ጤፍ እና በቆሎ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ምርጥ ዘሩ ከ34 ሺህ በላይ ለሆኑ አርሶአደሮች በግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በኩል ይከፋፈላል ተብሏል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ዓመት ብቻ 24 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በማውጣት ምርጥ ዘሮችን በድርቅ ለተጎዱ ወረዳዎች ማከፋፈሉ ተመላክቷል፡፡

በዚህኛው ዙር ያከፋፈለው ምርጥ ዘርም 5 ሺህ 663 ሄክታር መሬት በመሸፈን ከ160 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚያስገኝ ይጠበቃል፡፡

ይህም ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ በማስገኘት በድርቅ የተጎዱ አርሶ አደሮችን ያግዛል ነው የተባለው፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.