Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የክረምት ወቅት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የሶማሌ ክልል ሴቶችና ሕጻናት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀሊማ መሀመድ እና የሶማሌ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች እንዲሁም ወጣቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ ÷ ወጣቶች በአገር ጉዳይ ላይ በነቂስ በመሳተፍ ኢትዮጵያ ለያዘችው የብልጽግና ጉዞ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በበጎ ፈቃድ ተግባሩ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ተወላጅ ወጣቶች እንደሚሳተፉ እና የበጎፈቃድ ሥራውም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሁለት ወራት እንደሚቀጥል ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ወጣቶች በሚያከናውኑት የበጎ ፈቃድ ሥራ÷ በሰላም ግንባታ፣ በችግኝ ተከላ፣ በአቅመ ደካማ ቤት እድሳት፣ በደም ልገሳ፣ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ገቢ ማሰባሰብና ድጋፍ መስጠት ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.