Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ሳይንስ ካፌ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዳማ ሳይንስ ካፌ ያዘጋጀው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ ተከፈተ።
ዓውደ ርዕዩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት፡፡
በዓውደ ርዕዩ ላይም÷ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
ከቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች መካከልም÷ ትንሽ ጉልበት ያለውን ሞተር ጉልበቱን በማሳደግ የተሠራና በአንድ ሊትር እስከ 25 ኪሎ ሜትር መሄድ የሚችል መኪና፣ ከድንጋይ ወርቅ ማውጫ ማሽን፣ በሰዓት እስከ 40 ሺህ ኪሎ ግራም ቡና የሚያጥብ ማሽን፣ በቀን 200 ኩንታል በቆሎ መፈልፈል የሚችል የእህል መፈልፈያ ማሽን እንዲሁም አውቶማቲክ የመድሃኒት መርጫ ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም አውሮፕላን፣ ሰውሰራሽ አስተውህሎ፣ ከፋብሪካ የሚወጣ ጭስን ወደ ውሃ የሚቀይር ቴክኖሎጂ፣ የአቴንዳንስ መከታተያ ማሽን፣ አገልግሎቱን ከጨረሰ የመኪና ጎማ ነዳጅ ማምረት እና ከውጋጁ የድንጋይ ከሰልን የሚተካ ካርበን ማምረት፣ ተሽከርካሪ የማስታወቂያ ሰሌዳ፣ የአውቶሜሽን ስራዎች ለዕይታ ከቀረቡት ውስጥ ይጠቀሳሉ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ግንኝትን ለማሳደግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡
የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ወደ ምርትና አገልግሎት ቢቀየሩ ቴክኖሎጂን የሚያሻግሩ እና ሀብት የሚፈጥሩ መሆናቸውን ጠቁመው÷ የፈጠራ ስራዎቹ ወደ ማህበረሰቡ እንዲገቡ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.