Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከልማት አጋሮች ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚደረገው ድጋፍ ላይ ከልማት አጋሮችን ጋር ምክክር አካሄደ፡፡

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ እስካሁን የሠራቸውን ተግባራትና በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ለልማት አጋሮች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ፥ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የተለያዩ የፖለቲካ፣ የአመለካከት ፣ የሃሳብ ልዩነቶች ብሎም አለመገባባቶች በሰፊ የህዝብ ውይይቶች ሊፈቱ እንደሚገባ መንግስት በጽኑ ያምናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታዋ እንደገለፁት ፥ ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ውይይት ማካሄድ በሀገሪቱ ላይ የተደቀኑ ፈተናዎችን ለመቋቋም እንደሚያስችል ተናግረው ስራውን የተቀናጀና ተቋማዊ ማድረግን ይጠይቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ለኮሚሽኑ የሚደረጉ የልማት ድጋፎችን የትረስት ፈንድ በማቋቋም እንዲያስተባብር ውክልናም ሰጥቷል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም፥ በቀጣይ ለኮሚሽኑ በሀብት አሰባሰብና በፈንድ አስተዳደር ዙሪያ ድጋፍ ያደርጋል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.