Fana: At a Speed of Life!

በ45 የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ቴንዘ ቀበሌ ትምህርት ቤትን እንደ ካምፕ ሲጠቀሙ በነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ 45 የቡድኑ አባለት መደምሰሳቸው ተገለፀ።
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሸኔ ታጣቂዎች ላይ እየወሰዱ በሚገኘው ተከታታይ እርምጃ ትናንት ማለዳ አካባቢ በተከናወነው ዘመቻ ከተደመሰሱት 45 የሸኔ ታጣቂዎች በተጨማሪ ሁለት የቡድኑ አባላትና 35 ክላሽ እንኮቭ ጠመንጃዎች መማረካቸውን ምንጮችን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢላ ወረዳ ቢሎ እና ጎቤ በተባሉ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው የአሸባሪው የሸኔ ቡድንም÷ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደበት የሚገኘውን የተጠናከረ እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ተፍረክርኮ እየተበታተነ እንደሚገኝም እና ቡድኑ ቦታ ለመቀየር እየሞከረ መሆኑንም ተጠቁሟል፡፡
መንግስት በሕዝብ ላይ ሽብር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ በሚገኘው አሸባሪ ቡድን ላይ የተጠናከረ ሕግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.