Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፍ አጋርነት የትምህርት ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አቀፍ አጋርነት የትምህርት ልዑካን ቡድን ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ።

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የዓለም አቀፍ አጋርነት ለትምህርት ዋና ስራ አስፈፃሚ አሊስ ኦልብራይትና ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የዓለም አቀፍ አጋርነት ለትምህርት ልዑክ በሶስት ቀናት ቆይታው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከዓለም ባንክ፣ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር እና ከትምህርት ዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዓለም አቀፍ አጋርነት ለትምህርት ሃብት በማሰባሰብ ለኢትዮጵያና ለሌሎች ታዳጊ ሃገራት በትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.