Fana: At a Speed of Life!

ለፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያ ሳንሆን ራሳችንን ከጽንፈኝነት አርቀን የእህትማማችነትና ወንድማማችነት መርሐችንን ይበልጥ ወደ እያንዳንዱ ሰው እንዲደርስ በቁርጠኝነት እንሰራለን- የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያ ሳንሆን ራሳችንን ከጽንፈኝነት አርቀን የእህትማማችነትና ወንድማማችነት መርሐችንን ይበልጥ ወደ እያንዳንዱ ሰው እንዲደርስ በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲል የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አስታወቀ፡፡
በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ÷ ለቀጣይ ሊጉን ሊመሩ እና ሊያሻግሩ የሚችሉ አመራሮችን በመምረጥ እና ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
የአቋም መግለጫው÷ አገራዊ የምክክርና የውይይት መድረክ ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን ሴቶች በተሰማሩበት መስክ ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክቷል፡፡
በቀጣይ ዓመት ይጀመራል ተብሎ የሚታሰበውን ሀገራዊ የምክክርና የውይይት መድረክ ይበልጥ ስኬታማ ሆኖ ሀሳባችንን የምንገልጽበት የሌሎችንም ሀሳብ የምናዳምጥበት እንዲሆን ከወዲሁ ሴቶች ባላቸው ማህበረሰባዊ ቦታ ተጠቅመው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ይህን ለዛሬዋና ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ መፈጠር ትልቅ ሚና ያለውን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማጠልሸት ብዙዎች በርካታ እንቅፋቶችን ሲደረድሩ እንደሚስተዋል ገልጾ÷ ፈተናዎቹን ተራምደን ካሰብነው ለመድረስ ያስችለን ዘንድ የታቀደው የሀገራዊ ምክክር መድረክ ውጤታማ እንዲሆን የድርሻችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን ብሏል ጉባኤው በመግለጫው፡፡
እስከ ቀጣይ ጉባኤ እንዲተገበሩ አቅጣጫ የተቀመጠባቸውንና ሌሎችንም ተግባራት ከግብ ለማድረስ የበኩላችንን እንወጣለን ሲል የሊጉ ጉባኤ በመላው የኢትዮጵያ ሴቶች ስም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.