Fana: At a Speed of Life!

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የሰላምና የልማት ፎረም የችግኝ ተከላ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባለሀብቶችና የሥራ ፈጣሪዎች ትብብር የተመሠረተው የሰላምና የልማት ፎረም እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የፎረሙ የበላይ ጠባቂዎች የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያና የኮሚሽኑ ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የችግኝ ተከላው “ኑ ሰላምን እንትከል፣ ኑ እርቅን እንትከል፣ ኑ እድገትን እንትከል፣ ኑ እህትማማችነትን፣ ወንድማማችነትን እንትከል ኑ እንወያይ” በሚል መሪ መልዕክት ነው የተካሄደው።

የሰላምና የልማት ፎረሙ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ÷ በዚህ ወቅት እንዳሉት ለሀገራችን ሰላምና የአረንጓዴ ልማት በእጅጉ  ያስፈልጋታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ለሰላም ሊሰሩ ይገባል ነው ብለዋል።

የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ‘ዐሻራችን ለትውልዳችን’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.