Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በቀን 86 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በቀን 86 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት በነገው ዕለት በይፋ እንደሚመረቅ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
 
ፕሮጀቱ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት ተመድቦለት የተገነባ የመጀመሪያው ትልቅ የከርሰ ምድር የውሃ ፕሮጀክት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
የግንባታ ወጪውም በከተማ አስተዳደሩ በጀት የተሸፈነ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ፕሮጀክቱ ከ860 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.