Fana: At a Speed of Life!

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ2015 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከክልል ቢሮዎች እና ተጠሪ ተቋማት ጋር በመጪው በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ እየተወያየ ነው፡፡
 
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ዘርፉ ከተለመደው አሰራር ወጣ ባለ እይታ አዲሱን ነበራዊ ሁኔታ መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለበት የሚያስገነዝብ የአቅም ግንባታ ጊዜ ነበረን ብለዋል።
 
የተጀመረው አገራዊ የዴሞክራሲ ጉዞ እና ዘለቄታዊ አዲስ እሳቤ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ መቅረቡን የጠቆሙት ሚኒስትሯ ÷ በዚህም በርካታ ቁልፍ ጉዳዮች መነሳታቸውን ገልጸዋል፡፡
 
የቴክኒክና ሙያ ተቋሞቻችንን ከማስልጠን በላይ መመልከት፣ ጥራት ያለው የስራ ዕድል መፍጠር፣ የአስሪ እና ሰራተኛ ስምምነትን ከማረጋገጥ በላይ በአዲስ የኢንዱስትሪ ባህል ለምርታማነት መትጋት እና ግጭትን ተከትሎ የተፈጠሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ወደ መልካም ዕድል የመቀየር አስፈላጊነት ላይ ውይይት መደረጉንም አንስተዋል፡፡
 
በመድረኩ ቀጣይ እንደ አገር የተተለሙ የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ መዋቅራዊ ማሻሻያ እና የዘርፎች ማሻሻያ አሻግረው የሚመለከቱ ግቦች ላይ ምክክር መደረጉንም አመልክተዋል፡፡
 
ፋታ የማይሰጡ ባለብዙ ግንባር ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከፍተኛ ለውጥ እንደመጣ እና ትክክለኛው የዕድገትና ብልፅግና ጎዳና ላይ እንደምንገኝ ገምግመናል ነው ያሉት ሚኒስትሯ፡፡
 
የግሉ ዘርፍ ሚና ማደግ፣ የባንኮች አቅም ላይ ከፍተኛ ውጤት መታየት፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ችግር መቃለል፣ የገቢ መጨመር፣ የውጪ ምርት መጨመር ፣ የግብርና ተከታታይ ዕድገት፣ የማዕድን ዘርፍ ልማት እና ሌሎች ለውጥ የመጡባቸው ሁኔታዎች እንደማሳያ መነሳታቸውንም አክለዋል፡፡
 
አሁን ላይም በመድረኩ የለውጡ መሠረታዊ እሳቤ የሆኑ እንደ ሰው ተኮር መሆን፣ ማህበራዊ እሴቶቻችንን ማዳበር እና የተግባር ጥምረት ላይ ያተኮረ ገንቢ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.