Fana: At a Speed of Life!

የግብር ስርዓቱ ከሰው ንክኪ እየራቀ እና እየዘመነ መሄድ አለበት -ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 በጀት ዓመት የግብር የንቅናቄ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
 
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራን ጨምሮ ሌሎች የከተማው አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎችና የግብር ከፋዮች ተገኝተዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2014 በገቢ አሰባሰብ ለታየው መልካም አፈፃፀም እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
የገቢ እድገቱም ባለፉት ዓመታት በ2013 መጨረሻ የ11 ቢሊየን እድገት እንዲሁም በ2014 ዓ.ም ደግሞ የ23 ቢሊየን እድገት መመዝገቡን አውስተዋል፡፡
 
የገቢ እድገታችን ሲረጋገጥ በጀታችን ያድጋል፤ህዝባችን ልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመመለስ አቅማችንም ያድጋል ያሉት ከንቲባ አዳነች÷ ነገር ግን የአዲስ አበባ ግብር የመሰብሰብ አቅም ከዚህ በላይ መሆኑን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ጠቁመዋል፡፡
 
ተቀናጅተን ገቢ አሰባሰቡን በማዘመንና ፍትሃዊ በተለይም ባለድርሻ አካላት የጋራ አሰራር ስርዓት ዘርግተን ልናሳካው ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
 
በቀጣይም የታክስ መሰረቱን ማስፋት፣ የንብረት ህግ ግብር አስመልክቶ ተቋሙ ራሱን ዝግጁ ማድረግ አለበት፣ ግብር ከፋዩ ራሱ ወቅቱን ጠብቆ ግብሩን እንዲከፍል ማድረግ፣ የህግ ማስከበር ስራችንም ማጠናከር እና ተቋሙ በሰው ሃይል በግብዓትና ቴክኖሎጂ መጠናከር ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
 
የግብር ስርቱ ከሰው ንክኪ እየራቀ እየዘመነ መሄድ እንደሚኖርበት ተቁመው÷ የሰው ንክኪ ካለበት በሙስና ብልሹ አሰራር ለብክነት የሚዳረግ ይሆናል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የከተማ አስተዳደሩ በገቢ ግብር ላይ ያሉ ሰራተኞችንም ለማበረታታት የዚህን ወር ጥቅማ ጥቅም በእጥፍ እንደሚያሳድግም በመድረኩ ገልፀዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ በበኩላቸው ÷የከተማው አስተዳደሩ በጀት አምና ከነበረው 70 ቢሊየን ዘንድሮ ወደ 100 ነጥብ 5 ቢሊየን ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
በተያዘው በጀት ዓመት በአካል በመንቀሳቀስ ታማኝ ግብር ከፋዮችን የማበረታታትና እውቅና የመስጠት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.