Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከየትኛውም የዓለማችን አየር መንገዶች በላቀ አፍሪካ እና እስያን እያገናኘ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከየትኛውም የዓለማችን አየር መንገዶች በላቀ አፍሪካ እና እስያን እያገናኘ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነኀሤ ወር ላይ መካከለኛው ምስራቅን ሳይጨምር ወደ 13 የእስያ ሀገራት በረራ ለመጀመር ማቀዱ ተገልጿል፡፡

አየር መንገዱ የሕንድ ከተማ በሆነችው ቼናይ የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ጀምስ ፒርሰን ለሲምፕል ፍላይንግ በጻፈው መረጃ የጠቆመ ሲሆን አሁን ላይ ለመንገደኛ ተሳፋሪዎችም አገልግሎት መሥጠት መጀመሩን ከዓየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዛሬ አምሥት ሠዓት ላይ ወደ ህንድ ቼናይየሚያደርገው በረራ አራተኛው ነው ተብሏል።

በሣምንት ሦስት ጊዜ በረራ እንደሚኖርም ነው ዓየር መንገዱ የጠቆመው፡፡

በሐምሌ ወርም ወደ ጃካርታ በረራ እንደሚጀምር ነዉ የተጠቆመው።

በፈረንጆቹ 2019 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከየትኞቹም አየር መንገዶች በላቀ ሁኔታ በእስያ እና በአፍሪካ አኅጉራት ግንባር ቀደሙ ተመራጭ አየር መንገድ ሆኗል፡፡

ከ8 ሚሊየን በላይ በሁለቱ አህጉራት መካከል ከተጓዙ መንገደኞች መካከል ሩብ ያህሉ የኢትዮጵያን አየር መንገድን መጠቀማቸው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቼናይ፣ ጃካርታ እና ማኒላ የሚያደርገውን የመንገደኞች በረራ በቅርቡ እንደሚጀምርም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.