Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ከ60 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎች የአብሮነት ማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷መርሐ ግብሩ በአጠቃላይ ከ126 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በማዕድ ማጋራቱ እየታደለ ያለው አቅርቦት ዘይት፣ ዱቄት፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ፣ በከተማ ግብርና የተመረቱ የጓሮ አትክልቶችና ሌሎች የፍጆታ እቃዎች ናቸው ብለዋል ።

ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ አብሮነታችንን በማጠናከር፣ መደጋገፍና መረዳዳት ባህላችንን ማሳደግ ይገባል፤ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ይሰራል ነው ያሉት።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.