Fana: At a Speed of Life!

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 510 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 510 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስምርቋል።
 
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የኢፌዴሪ መስኖና ቆላመ አከባቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ እና ሴኔት አባላት ተገኝተዋል።
 
የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ዩኒቨርሲቲው በምርምር፣ በመማር ማስተማርና ማህበረሰብ አቀፍ ተልዕኮዎች የተለያዩ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ዓመታት ከ26 ሺህ በላይ ምሩቃንን በተለያዩ የሙያ መስኮች አስተምሮ ለአገር የተማረ የሰው ኃይል ልማት ማበርከቱንም አንስተዋል ።
 
በዘንድሮው ዓመት ብቻ 8 ሺህ ተማሪዎችን አስመርቋል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ።
 
ዩኒቨርሲቲው በአሁን ወቅት በ58 የመጀመሪያ፣ በ42 የሁለተኛ እና በሁለት የሶስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብሮች ከ27 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.