Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 11 የድምፃውያን ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ቴሌቪዥን የሚዘጋጀውና ተወዳጁ የፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር 11ኛ ምዕራፍ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።

ፋና ላምሮት ከአዳዲስ ተወዳዳሪዎችና ባለተሰጥኦዎች ጋር በቀጥታ ስርጭት የጀመረ ሲሆን፥ በሁለት ምድብ የተከፈሉት የምዕራፍ 11 ተወዳዳሪዎች 12 ናቸው፡፡

ለዘጠኝ ሳምንታት የሚቆየው የምዕራፍ 11 የፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር መጨረሻ የሚቀሩ አራት የምዕራፉ ተፋላሚዎች እንደየደረጃቸው የ500 ሺህ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

አንደኛ ደረጃን ላገኘ የ200 ሺህ ብር፣ 2ኛደረጃ 150 ሺህ ብር፣ 3ኛ ደረጃ 100 ሺህ ብር እና 4ኛ ደረጃን ያገኘ የ50 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ ይሆናሉ፡፡

በተጨማሪም የፍጻሜ ተወዳዳሪዎቹ በጉጉት ለሚጠበቀው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

በቀጥታ ስርጭት የተጀመረው የምዕራፍ 11 የፋና ላምሮት ውድድር ተመልካቾች ወደ 8222 አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ለሚደግፉት ተወዳዳሪ ድምፅ መስጠት ይችላሉ።

የምዕራፍ 10 ፋና ላምሮት የባለተሰጥዖ ድምጻውያን ውድድር ፍጻሜ ከሁለት ሳምንት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ተወዳዳሪዎች ራሳቸው በመረጧቸው እና ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ተፈትነው ከአንድ እስከ አራት ለወጡት ተወዳዳሪዎቹ በአጠቃላይ የ500 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ያለምወርቅ ጀንበሩ የ10ኛው ምዕራፍ አሸናፊ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.