Fana: At a Speed of Life!

ለራስ ቴአትር ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለራስ ቴአትር ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

አንጋፋውና በኢትዮጵያ የጥበብ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው በርካታ አንጋፋ አርቲስቶችን ለሀገር ያበረከተው የራስ ቴአትር ቤት አዲስ ግንባታ ነው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር ቤት ግንባታ እንዲሁም ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ህፃናትና ወጣቶችን ቴአትርና ሃገር ፍቅር ቴአትር ቤቶችን ግንባታ እያጠናቀቀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዛሬው ዕለት በግንባታ መሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ላይ ታዋቂዎቹ አንጋፋዎቹ የኪነጥበብ ሰዎች በኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ውጣ ውረድ ውስጥ ትልቅ ዋጋ የከፈሉ አርቲስቶች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት ለኪነጥበቡ ልዩ ትኩረት በመስጠት በመስራት ላይ እንገኛለን፤ በከተማችን 10 አምፊ ቴአትሮችን በማስገንባት የማዘጋጃ ቤቱ የባህል አዳራሽ ባማረ መልኩ የገነባን ሲሆን ፥ ዛሬም የመጀመሪያውን አዲስ ቴአትር ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠናል ብለዋል፡፡

የማንጨርሰውን አንጀምርም ፤ ይህንንም እንጨርሳለን ያሉት ከንቲባ አዳነች ፥ ጥበብ ትውልድን በመቅረፅና በመገንባት ትልቅ ሚና ስላላት አሁንም ትኩረት ሰጥተን መስራታችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት።

አክለውም እናንተም ጥበባችሁን ተጠቅማችሁ ሀገር ግንባታ ላይ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ላይ በርትታችሁ ስሩ በማለት መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.