Fana: At a Speed of Life!

ከዒድ እስከ ዒድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት የሁለተኛው ምዕራፍ ስኬታማ እንዲሆን ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛውን ምዕራፍ ከዒድ እስከ ዒድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤትን ስኬታማ እንዲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ።
የጉዞ መረሐ ግብሩ ከሰኔ 28/2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ የዳያስፖራ አገልግሎት አስታውቋል።
ዒድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪውን መርሐ ግብር በበላይነት እየመራ እና እያስተባበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ሲሆን ፥ ጥሪውን ተከትሎም በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት መምጣታቸውን የዳያስፖራ አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
ጥሪውን እንዲያስተባብር የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ቀጣዩ ምዕራፍ ከዒድ እስከ ዒድ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲጀመር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ሁለተኛው ምዕራፍ በተሳካ ሁኔታ ማከናወን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ማድረጉንም አገልግሎቱ አስታውቋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የነበሩ ክፍተቶን ለመቅረፍ በሁለተኛ ዙር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው እንደሚገባ ውይይት መደረጉን ከዳያስፖራ አገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.