Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ21ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል የፖሊስ አባላት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ21ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል የፖሊስ አባላት በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ21ኛ ዙር በአዋሽ መሰረታዊ ፖሊስ ስልጠና አካዳሚ ለረጂም ጊዜ ያሰለጠናቸውን በርካታ ምልምል የፖሊስ አባላትን ነው በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት ያስመረቀው።
የእለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሲሆኑ ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት የሀገራችን ፖሊስ በየስርዓቱ እየወደቀ እየተነሳ ሲያገለግል የቆየ ተቋም ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።
በተለይም ባለፉት 27 ዓመታት ሙያዊ እና ተቋማዊ ሆኖ እንዲገነባ ሳይሆን የቡድኖችን ፍላጎት የሚጠብቅ ሆኖ እንዲያገለግል በአንፃሩ በዜጎች ዘንድ የሚፈራ እና የስጋት ተቋም ሆኖ አልፏልም ነው ያሉት።
በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሎችና በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች መገኘታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.